የአብይ አገዛዝ በአማራ ክልል ቴሌኮም መዝጋቱ ያደረሰዉን ሁለተናዊ ጉዳት እያጠና ሲሆን ለዚሁ ጥናት ይህንን መጠየቅ እንድትሞሉ ይጠይቃል።
እንኳን ወደ አክሰስ ናው የኢንተርኔት አገልግሎት መቋረጥ ልምምዶች ፕሮጀክት በደህና መጣችሁ፡፡ ከዚህ በፊት የኢንተርኔት አገልግሎት መቋረጥ ከደረሰባችሁ ልምዳችሁን መስማት እንፈልጋለን፡፡ ይህ የሞባይል ኢንተርኔት፣ የመስመር ኢንተርኔት፣ የስልክ አገልግሎት ወይም እንደ ዋትስአፕ፣ ትዊተርና ፌስቡክ የመሳሰሉ አፕሊኬሽኖች መቋረጥን ያጠቃልላል፡፡ ለአክሰስ ናው የምታጋሩት ልምድ በ#KeepItOn Coalition (የኢንተርኔት አይጥፋ ጥምረት ሃሽታግ) በኩል የኢንተርኔት አገልግሎት መቋረጥን ለመዋጋት ይረዳናል፡፡ ልምዳችሁን በድረገጻችን ወይም በሚድያ ድርጅት በኩል ልናቀርበው እንችላለን፡፡ ማንነታችሁን ለመግለጽ የማትሹ ከሆነ ፍላጎታችሁን እናከብራለን ስለዚህም ልምዳችሁን በተለዋጭ ስም እንቀበላለን፡፡ ሌሎችንም በመወከል የእነርሱን ልምድ ማካፈል ትችላላችሁ፡፡ ይህንን ፎርም ለመጠቀም የማትፈልጉ ከሆነና፣ በኢሜይል ልምዳችሁን ለማካፈል ከፈለጋችሁ ወይም ጥያቄ ካላችሁ ይህን የኢሜይል አድራሻ ተጠቀሙ፡፡ felicia@accessnow.org (PGP: https://keys.accessnow.org/felicia.asc)
አማረኛ ለመሙላት:
Comments