top of page

የአብይ አህመድ አገዛዝ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን (ኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ) ላይ እያካሄደው ያለውን ጦርነት አስመልክቶ የተሰጠ መግለጫ

Writer: AAA-adminAAA-admin

መግለጫ

ጥር 29 ቀን 2015



የአማራ ማህበር በአሜሪካ (AAA) የዐቢይ አህመድ አገዛዝ በሃይማኖት መሪዎች ላይ እያደረሰ ያለውን ግፍ እና

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንን ለመከፋፈል የሚያደርገውን ሙከራ በጽኑ ያወግዛል። አብይ

አህመድ አሊ ወደ ስልጣን ከመጣ በኋላ በኦሮሞ ብልፅግና ፓርቲ አማካይነት በአጭር ጊዜ ውስጥ የኦሮሞ

የበላይነትን ለመገንባት፣ ከዚያም በኋላ በኢትዮጵያ እና በህዝቦቿ ላይ የኦሮሞ ሪፐብሊክን ለመገንባት ሲጥሩ

ቀውሶችን በማምረት ላይ ተጠምደዋል። በውጤቱም፣ ለዚህ የተሳሳተ፣ ወንዝ የማያሻግር እና በጥላቻ ላይ

የተመሰረተ ዓላማ እንቅፋት ነው ብለው የሚያምኑት ማንኛውም አካል የእስርና የእንግልት ዒላማ ሆኗል። የስሞኑ

በኢ/ ኦ/ተ/ቤ/ክ ላይ በመንግስት የተደገፈ ጥቃት፣ የአብይ መንግስት የኢትዮጵያን መሰረታዊ ተቋማት እና

ምልክቶች የማፍረስ አላማ ቀጣይነት ማሳያ ነው። ይህ የኦሮሞ ሪፐብሊክን የመገንባት ፕሮጀክት በኦሮሚያ ክልል

ለአስርት አመታት የዘለቀውን የአማራ የዘር ማጥፋት ወንጀል ሰለባዎች ቁጥር በከፍተኛ ደረጃ እንዲጨምር

ከማድረጉም በላይ፤ አንድነትን በሚያበረታቱ እንደ ኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ እና ተከታዮቿ (ኦርቶዶክስ ክርስትያን ኦሮሞዎችን

ጨምሮ) ላይ ተደጋጋሚ የጥቃት ኢላማ ተደርገዋል።


አብይ አህመድ ለባለሟሎቹ ከተወገዙት ጳጳሳት ጋር በተያያዘ በቅርቡ የሰጠው መመሪያ ጉዳዪ ፖለቲካዊ እንደሆነ የሚያረጋግጥ ሲሆን በመካሄድ ላይ ያለውም በመንግስት የሚደገፍ የኢትዮጲያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያንን በኦሮሞ አክራሪ ብሄርተኞች አማካኝነት የመቀራመት ድርጊት ለአለፉት አስርት አመታት ሲሰሩት የቆዩት የፖለቲካ ፕሮጀክት ተቀፅላ ነው። ይህ በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ ውስጥ ታይቶ የማይታወቅ ጣልቃገብነት እና የመሠረታዊ እሴቶችን መበከል ኢትዮጵያ ከቀን ወደ ቀን ፍፁም ወደ አምባገነንነት እየወረደች መሆኗን ና በሺህ ዓመታት ታሪኳ ታይቶ በማይታወቅ ደረጃ የህልውና ስጋት ውስጥ መውደቋንም የሚያሳይ ነው። በመሆኑም ሁሉም አማራ እና ኢትዮጵያዊያን ለሁሉም ሁኔታዎች ዝግጁ እንዲሆኑ የአማራ ማህበር በአሜሪካ (AAA) በጽኑ ያሳስባል።


የአማራ ማህበር በአሜሪካ (AAA) እኩልነትን እና ዲሞክራሲን የሚያበረታታ ማንኛውንም እንቅስቃሴ ለመደገፍ ሁሌም ዝግጁ ነው። አለምአቀፍ ተዋናዮች በኢትዮጲያ ያለውን ሁኔታ ክብደት በመረዳት ኢትዮጲያውያን ጠ/ሚ አብይ አህመድ አሊ እና የኦሮሚያ ክልል ፕሬዝዳንት ሽመልስ አብዲሳ በሀገሪቱ አስፈላጊ ለሆነው የዳግም ጅማሮ፣ እውነተኛ ውይይት፣ እርቅና ተጠያቂነት ሲባል ከመንበረ ስልጣናቸው እንዲወርዱ እያቀረቡት ያለውን ጥያቄ እንዲቀላቀሉ ጥሪውን ያስተላልፋል።





Comments


Share this  site on Twitter

  • Facebook
  • Twitter

©2021 by Amhara Association of America.

bottom of page