top of page

በአማራ ክልል ጎጃም የንፁሀን ዜጎችን ሕይወት የቀጠፈውን የሰው አልባአውሮፕላን ጥቃትን በተመለከተ የተሰጠ የሐዘን እና የውግዘት መግለጫ

  • Writer: AAA-admin
    AAA-admin
  • 2 minutes ago
  • 1 min read


በአማራ ክልል ጎጃም የንፁሀን ዜጎችን ሕይወት የቀጠፈውን የሰው አልባ አውሮፕላን ጥቃትን በተመለከተ የተሰጠ የሐዘን እና የውግዘት መግለጫ


በምስራቅ ጎጃም ዞን በእናርጅ እናውጋ ወረዳ በገደብ ቀበሌ ሚያዚያ 9 ቀን 2017 በሰው አልባ አውሮፕላን ጥቃት የበርካታ ሰዎች ሕይወት እንደተቀጠፈ በተሰማው ዜና እጅግ አዝነናል። በዚህ ዘግናኝ ጥቃት ለተጎዱ ቤተሰቦች እና ማህበረሰቦች የተሰማንን ጥልቅ ሀዘን እንገልፃለን። እንዲህ ዓይነቱን የጅምላ ሕይወት መጥፋት ትክክል የሚያደርግ ምንም ዓይነት ምክንያት ሊኖር አይችልም።


ይህ በአብይ አህመድ የሚመራው አገዛዝ የተፈጸመው ዘግናኝ ድርጊት በሰው ልጆች ላይ የተፈፀመ አሳዛኝ ጭፍጨፋ ብቻ ሳይሆን የዓለም አቀፍ የሰብአዊ መርሆችን መጣስም ጭምር ነው። የተፈፀመው ተመጣጣኝ ያልሆነ የኃይል እርምጃ፣ ሕዝብ በሚበዛባቸው አካባቢዎች ላይ ማነጣጠር እና የንፁሀን ዜጎችን ህይወት አለመጠበቅ አስቸኳይ ምርመራ እና ተጠያቂነትን የሚሹ ተግባራት ናቸው። ማኅበራችን ባወጣቸው የተለያዩ ዘገባዎች እና በበርካታ የሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች እንደተዘገበው በአማራው ጦርነት በሰላማዊ ዜጎች ላይ እየደረሰ ያለው የሰው አልባ አውሮፕላኖች ጥቃት የአብይ አገዛዝ ስልታዊ በሆነ መንገድ በአማራዎች ላይ እየወሰደ ያለውን የዘር ማጥፋት ድርጊት የሚያሳይ ነው። በሚያዝያ 2015 በአማራ ላይ ጦርነት ከተቀሰቀሰበት ጊዜ ጀምሮ በሰላማዊ ሰዎች ላይ ያነጣጠሩ 184 የሰው አልባ አውሮፕላን ጥቃቶችን መዝግቧል።


ይህ ግፍ በገለልተኛ አካላት ምርመራ እንዲደረግበት እና የአብይ አገዛዝ የሰው አልባ አውሮፕላን አብራሪዎችን ጨምሮ በድርጊቱ የተሳተፉ አካላት በሙሉ በህግ እንዲጠየቁ እናሳስባለን። በአማራው ጦርነት ላይ የሰው አልባ አውሮፕላኖችን በመደበኛነት መጠቀም ሊቆም ይገባል።


ከሕዝብ ጋር በሀዘንና በአብሮነት ቆመን ለዚህ መቼም ለማንረሳው ድርጊት በፍትህን እንጠይቃለን።





 
 

 
 
 

Comments


Share this  site on Twitter

  • Facebook
  • Twitter

©2021 by Amhara Association of America.

bottom of page