top of page

የአብይ አገዛዝ በአማራ ላይ ባወጀው የአማራ ጦርነት በሚሊዮን የሚቆጠሩሕጻናት ከትምህርት ገበታ የተገለሉ ሲሆን በሺዎች የሚቆጠሩ ትምህርትቤቶች ሥራቸውን አቁመዋል

  • Writer: AAA-admin
    AAA-admin
  • 23 hours ago
  • 2 min read

April 10, 2025 Miyazia 2, 2017 E.C.



የአብይ አገዛዝ በአማራ ላይ ባወጀው የአማራ ጦርነት በሚሊዮን የሚቆጠሩሕጻናት ከትምህርት ገበታ የተገለሉ ሲሆን በሺዎች የሚቆጠሩ ትምህርትቤቶች ሥራቸውን አቁመዋል


ሚያዝያ 2 ቀን 2017 ዓ.ም. የአማራ ማኅበር በአሜሪካ በኢትዮጵያ እየተካሄደ በሚገኘው የአማራ ጦርነት ውስጥ ባለው የትምህርት ሁኔታ ላይ ልዩ የምርመራ ዘገባ አውጥቷል። ይህ ሪፖርት ጦርነት እና ፖለቲካዊ ሁከት በትምህርት አሰጣጥ እና በአካባቢው የትምህርት መሠረተ ልማቶች ላይ ያሳደረውን ተጽዕኖ አጠቃላይ እይታ ለማቅረብ ያለመ ነው።


ይህ ዘገባ በወጣበት ወቅት የአማራ ክልል ከ4 ዓመታት በላይ በዘለቀ ያልተቋረጠ የብሔር ጦርነት ውስጥ ገብቶ ይገኛል። የቅርብ ጊዜው ጦርነት በክልሉ እና አጎራባች አካባቢዎች ከ30 በላይ ዋና ዋና ከተሞችን እና ከተሞችን አጠቃሎ በሚያዝያ 2015 ዓ.ም. የተካሄደ ክልላዊ ሕዝባዊ የተቃውሞ ሰልፎችን ተከትሎ የተፈጠረው የአማራ ጦርነት ነው። ሰልፈኞቹ በመላው ኢትዮጵያ በአማራ ተወላጆች ላይ እየደረሰ ያለው የዘር ማጥፋት፣ የዘር ማፅዳት፣ የፖለቲካ መገለል፣ የጉዞ ገደብ፣ ቤት ማፍረስና ማፈናቀል እና መሰል ድርጊቶች እንዲቆሙ ጠይቀዋል። የአማራ ሕዝብን ጥያቄዎች በመመለስ ፈንታ በሚያዝያ 2015 መገባደጃ ላይ በአብይ አህመድ የሚመራው የኦሮሞ ብልጽግና ፓርቲ አገዛዝ “በፅንፈኞች” ላይ የሚደረግ የሕግ ማስከበር ዘመቻ ብሎ በማወጅ ለ2 ተከታታይ ዓመታት በኦሮሞ ብልጽግና ወታደሮች (የገዥው ኃይሎች) እና በአማራ ፋኖ ራስን የመከላከል ኃይል መካከል ጦርነት እየተካሄደ ይገኛል። የትጥቅ ጦርነት ከጀመረበት ጊዜ አንስቶ ግጭቱ ወደ ሁሉም የክልሉ የአስተዳደር ዞኖች በመስፋፋት በሚሊዮን የሚቆጠሩ ነዋሪዎችን ክፉኛ ጎድቷል።


በጦርነቱ ሂደት ወቅት በመላው የአማራ ክልል እና ሌሎች የኢትዮጵያ አካባቢዎች በአገዛዙ ታጣቂዎች እጅ በአማራ ሰላማዊ ህዝብ ላይ የሚፈፀመውን ከፍተኛ የዓለም አቀፍ ሕግ ጥሰቶችን የአማራ ማኅበር በአሜሪካ እየሰነደ ይገኛል። ይህ በየቀኑ በሠላማዊ ሰዎች እና ትምሕርት ቤቶችን ጨምሮ በሲቪል ኢላማዎች ላይ በአገዛዙ ኃይሎች በሚደረግ ጥቃት በመቶ ሺዎች የሚገመቱ ሰዎች ሰለባዎች ሆነዋል። በአማራ ጦርነት ምክንያት 4.4 ሚሊዮን የሚገመቱ ተማሪዎች (60%) ከትምህርት ገበታ ውጪ የሆኑ ሲሆን ከ6,000 የሚበልጡ ትምህርት ቤቶች ላይ ጉዳት ደርሷል።


ይህ ዘገባ በአራት ክፍለ ሀገራት በሚገኙ 11 የዞን አስተዳደሮች ላይ ልዩ ትኩረት በማድረግ በአማራ የትምህርት ስርዓት ላይ የተፈጠሩ ተፅዕኖዎችን ለመለየት ሞክሯል። ዘገባው እንደገለፀው ከ 5,231 ትምህርት ቤቶች በላይ በፀጥታ ችግር፣ በትምህርት ቤት ህንጻዎች / ንብረቶች ላይ በደረሰ ውድመት እና ትምህርት ቤቶች ለወታደራዊ አገልግሎት እንዲውሉ በመደረጋቸውምክንያት ከ 3.5 ሚሊዮን በላይ ህጻናት ከትምህርት ቤት ውጭ ሆነዋል። ዘገባው የተዘጋጀው በአማራ ማኅበር በአሜሪካ የሰብዓዊ መብት መርማሪዎች ቡድን ሲሆን ይህም ከአንደኛ እና ሁለተኛ ደረጃ ምንጮች ጥምር መረጃን በማሰባሰብ የተጠናቀረ ነው። በክልሉ የግንኙነት መቋረጥ እና የጥቃት ፍርሃትን ጨምሮ የተለያዩ ተግዳሮቶች ቢኖሩም መረጃዎችን ማሰባሰብ ተችሏል።


በአጠቃላይ ይህ የቅርብ ጊዜ ዘገባ የክልሉ የትምህርት ሥርዓት በከፍተኛ ሁኔታ መበላሸቱን እና ይህም በሀገሪቱ የአሁን እና የወደፊት ትውልዶች ተስፋ ላይ ከፍተኛ ተጽእኖ እንደሚኖረው ያሳያል። በዚህ ዘገባ ግኝቶች ላይ በመመርኮዝ የአማራ ማኅበር በአሜሪካ ይህንን ችግር ሊያቃልሉ ለሚችሉ የዓለም አቀፍ ፖሊሲ አውጪዎች እና ለሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ተከታታይ ምክረ ሃሳቦችን አዘጋጅቷል። እነዚህ ባለድርሻ አካላት የአፍሪካ ህብረት፣ የተባበሩት መንግስታት የሰብዓዊ መብቶች ምክር ቤት (ዩኤንኤችአርሲ)፣ የተባበሩት መንግስታት የትምህርት፣ የሳይንስ እና የባህል ድርጅት (ዩኔስኮ) እና በአጠቃላይ ዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶችን ያጠቃልላል።


ሙሉ የምርመራ ዘገባዉን ያንብቡት






 
 
 
 

Comments


Share this  site on Twitter

  • Facebook
  • Twitter

©2021 by Amhara Association of America.

bottom of page