ጉዳዩ: የአሜሪካ የንግድ ችሮታ (አጎአ) ላይ የተጣለው እገዳ እንዲነሳ እና ሀገሪቱ ወደ አጎአ እንድትመለስ በኢትዮጵያ መንግስት የቀረበው ጥያቄ በአሜሪካ መንግስት ውድቅ እንዲደረግ ስለመጠየቅ፤
ክቡር አምባሳደር ታይ፣ ሎቢት፣ የአማራ ማህበር በአሜሪካ (AAA) 1 የተሰኘ የሲቪክ ድርጅት ህጋዊ ወኪል ሲሆን፣ ማህበሩ በኢትዮጵያ የአማራ ህዝብ ፖለቲካዊ ጥያቄዎች እና ሰብአዊ ጥቅሞችን ለማስከበር የተቋቋመ የሲቪክ ድርጅት ነው። እኔም ይህንን ጥያቄ በደብዳቤ ያቀረብኩት፣ የአማራ ማህበር በአሜሪካ እና በሰሜን አሜሪካ የአማራ ማህበራት ፌዴሬሽን (ፋና) የተሰኙ የሲቪክ ማህበራት ስብስብን በመወከል ነው። በዚህ መሰረት፣ በኢትዮጵያ ውስጥ በአማራ ህዝብ ላይ እየተፈጸመ የሚገኘው መጠነ ሰፊ የሰብአዊ መብት ጥሰት እስካልቆመ ድረስ፣ በአሜሪካ መንግስት ከሰሃራ በታች ላሉ የአፍሪካ ሀገራት ለሚሰጠው ከቀረጥና ኮታ ነጻ የሆነው የንግድ ችሮታ (አጎአ) ሀገሪቱ እንድትመለስ የኢትዮጵያ መንግስት ያቀረበው ጥያቄ ውድቅ እንዲደረግ በሚል ነው። ይህ ደብዳቤ የኢፌዲሪ መንግስት እ.ኤ.አ. በመጋቢት 2 ቀን 20232 ለጻፈው ደብዳቤ ግልጽ ምላሽ ይሰጣል።
እንደሚታወቀው ኢትዮጵያ በአጎአ ታገኝ የነበረው የንግድ ችሮታ፣ እ.ኤ.አ. ከጥር 1፣ 2022 ጀምሮ በአሜሪካ መንግስት ውሳኔ ታግዷል።3 ከዚህ ቀደም ብሎ እ.ኤ.አ. በህዳር 2፣ 2021፣ የአሜሪካው ፕሬዘዳንት ጆ ባይደን መግለጫ የሰጡ ሲሆን፣ “በአብይ መንግስት ሀይሎች እና በህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) መካከል በነበረው የትጥቅ ግጭት፣ ተፋላሚ ወገኖች "ዓለም ዓቀፍ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችን ስለፈጸሙ፣ ኢትዮጵያ ለአመታት ተጠቃሚ ከነበረችበት አጎአ ለመቀጠል ቅድመ ሁኔታ አላሟላችም በሚል ነበር።
በተመሳሳይ ቀን፣ የአሜሪካ የንግድ ተጠሪ የሆኑት (USTR) የአጎአ የንግድ ችሮታ እገዳው እንዲነሳ ስለሚያስፈልጉ ቅድመ ሁኔታዎች እና በኢትዮጵያ ያለው ሰብዓዊ ቀውስ በዘላቂነት እንዲፈታ በኢትዮጵያ መንግስት ሊወሰዱ በሚገባቸው እርምጃዎች ዙሪያ ግልጽ ማብራሪያ ሰጥተው ነበር።
የትጥቅ ግጭቱ ተፋላሚ ወገኖች የነበሩት የአብይ አገዛዝ እና ህወሓት በፕሪቶሪያ ዘላቂ ሰላምን ለማምጣት የተኩስ አቁም ስምምነት (COHA) ከተፈራረሙ ጀምሮ፣ ሁለቱም ወገኖች ለአጎአ እገዳ መነሻ ምክንያቶች ተቀርፈዋል የሚል ከነባራዊ እውነታው የራቀ እና የተሳሳተ ግምገማ በማሳየት፣ የኢትዮጵያ መንግስት ሀገሪቱ ላይ የተጣለው እገዳ እንዲነሳ ሲጎተጉት ቆይቷል።
ስምምነቱ የተፈረመው በፌደራል መንግስት እና በህወሀት መካከል አስቸኳይ እና ዘላቂ የተኩስ አቁም እንዲደረግ ነበር።7 ሆኖም፣ የአማራ ህዝብ ከCOHA ስምምነት ተሳታፊ እንዳይሆን በመደረጉ ምክንያት፣ የአማራ ህዝብ የረጅም ጊዜ ህጋዊ ጥያቄዎች የሆኑት ማለትም፣ በኦሮሚያ ክልል በአማራ ተወላጆች ላይ እየተፈጸመ ላለው የዘር ማጥፋት ወንጀል አለም አቀፋዊ ተጠያቂነት እንዲኖር እንዲሁም በወልቃይት እና በራያ አካባቢ ለሚነሳው የማንነት ጥያቄ ህጋዊ እውቅና እንዲሰጥ የሚሉ ወሳኝ ጉዳዮች ትኩረት ሳያገኙ ቀርተዋል። ይህ በንዲህ እንዳለ፣ የፕሪቶሪያው ስምምነት የኢትዮጵያ መንግስት ሊፈጽማቸው የሚገቡ ልዩ ቅድመ ሁኔታዎችን በዝርዝር ያስቀምጣል። ከእነዚህ መካከል፣ የሰብአዊ መብቶች ጥበቃ; ያልተገደበ የሰብዓዊ ዕርዳታ በመላ አገሪቱ እንዲተገበር፣ ተቋርጠው የነበሩ የስልክ እና ኢንተርኔት፣ የኤሌትሪክ እና የባንክ አገልግሎቶች እንዲጀመሩ፣ ጾታዊ ጥቃቶች እና በሴቶች ላይ የሚፈጸሙ የሰብአዊ መብት ጥሰቶች እንዲያስቆም፣ እርቅ እና ተጠያቂነትን ለማስፈን የሽግግር ፍትህ ፕሮግራም እንዲተገበር ማድረግ ናቸው።
በትግራይ ክልል ሲደረግ የነበረው የትጥቅ ግጭት የተኩስ አቁም ስምምነት መፈረሙን ተከትሎ የቆመ ቢሆንም፣ የፌደራል መንግስቱ እና ህወሓት በፕሪቶሪያ እ.ኤ.አ በህዳር 2 ቀን 2022 የተፈራረሙትን የሰላም ስምምነት አላከበሩም፤ ይልቁንም፣ እ.ኤ.አ. በሚያዚያ 2023 የአብይ መንግስት በአማራ ክልል ግልጽ ጦርነት መክፈቱን ተከትሎ በሀገሪቱ ያለው የሰብአዊ መብት ሁኔታ ከጊዜ ወደ ጊዜ እያሽቆለቆለ ይገኛል።
በተለይም ከግንቦት 2022 ጀምሮ፣ የአብይ መንግስት በአማራ፣ በኦሮሚያ ክልል እና በአዲስ አበባ ከተማ በሚኖሩ የአማራ ብሔር ተወላጅ የሆኑ በህዝብ ከፍተኛ እውቅና ያላቸው የመንግስት ተቃዋሚዎች፣ ጋዜጠኞች፣ የሲቪክ ማህበራት አመራሮች፣ የሰብአዊ መብት ተሟጋቾች እና አንቂዎች ላይ ያነጣጠረ ብሔር ተኮር ጥቃት አስገድዶ መሰወር እና የዘፈቀደ እስራት እና ሌሎች የሰብአዊ መብት ጥሰቶች መፈጸሙን አጠናክሮ ቀጥሏል።
በመቶዎች የሚቆጠሩ የአማራ ተወላጆች በአዋሽ አርባ፣ ቱሉ ዲምቱ (ሸገር ከተማ)፣ በፍቼ ከተማ ኮንዶሚኒየም እና በሌሎች ከሀገሪቱ ዋና ከተማ አዲስ አበባ ርቀው በሚገኙ ማጎሪያ ስፍራዎች በታሰሩበት በኮሌራ እና ተመሳሳይ ተላላፊ በሽታዎች እንደሞቱ ታውቋል።
እ.ኤ.አ. በነሃሴ 2023 በአማራ ክልል የታወጀውን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅን እንደምክንያት በመጠቀም የኢትዮጵያ መንግስት በክልሉ የስልክ እና የኢንተርኔት አገልግሎቶች ላይ ገደብ በማድረግ በክልሉ ስላለው የሰብአዊ ሁኔታ መረጃዎች እንዳይወጡ አድርጓል።10 ይህ እንደተጠበቀ ሆኖ፣ ተአማኔ ከሆኑ የሚዲያና የሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች የሚወጡ ሪፖርቶች፣ በአማራ ህዝብ ላይ የሚፈጸሙ የሰብአዊ መብት ጥሰቶች ከጊዜ ወደ ጊዜ በመጠን እየጠነከረና ድግግሞሹም እየጨመረ መቀጠሉን ያረጋግጣሉ።
ለአብነት ያህል በመንግስት በጀት የሚንቀሳቀሰው የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ያወጣቸው ተከታታይ ሪፖርቶች እንደሚያሳዩት፣ የአብይ አህመድ አገዛዝ የተለያዩ ጥቃቶችን ማለትም፣ የጅምላ እስራት፣ ያለፍርድ የሚፈጸሙ መጠነ ሰፊ ግድያዎች፣ በድሮን እና በከባድ መሳሪያ በሰላማዊ ሰዎች ላይ እየደረሱ ያሉ ጥቃቶች፣ ጾታን መሰረት ያደረጉ ትንኮሳዎች እና ጾታዊ ጥቃቶች፣ የሰብአዊ ዕርዳታ ማቋረጥ እና የኢንተርኔት አገልግሎት ሙሉ ለሙሉ ማቋረጥ አሁንም ተባብሰው ቀጥለዋል።11 ኢሰመኮ የአብይ ስርዓት ሃይሎች በአማራ ክልል በምስራቅ ጎጃም ዞን ደብረማርቆስና መርጦለመርያም፣ በምዕራብ ጎጃም ዞን ጂጋ፣ በሰሜን ጎጀም ዞን አዴትና መራዊ ፣ በደቡብ ጎነደር ዞን ደብረታቦር፣ በማዕከለዊ ጎንደር ዞን ደልጊ፣ በሰሜን ሽዋ ዞን ማጀቴ፣ ለሚ፣ ሽዋሮቢትና አንጾኪያ ንጹሃንን ኢላማ ያደረገ ጥቃት መፈጸማቸዉን ሪፖርት አድርጓል፡፡12መጠነሰፊ የሆነና ህግን መሰረት ያላደረገ የንጹሃንና ጋዜጠኞች እስርም ተባብሶ ቀጥሏል፡፡ ኢሰመኮ በአማራ ክልል በባህርዳር፣ ጎንደር፣ ቆቦ፣ ላሊበላ፣ ደብረታቦር፣ ደብረማርቆስ ፣ ፍኖተሰላም ፣ መካነሰላም እና ሽዋሮቢት ከተሞች እንዲሁም በኦሮሚያ ክልል ሸገር ከተማ እና በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የዘፈቀደ እስሮች መፈጸማቸዉን በሪፖርቱ አመላክቷል፡፡
ንጸሃንንና የህዝብ አገልግሎት መስጫ ተቋማትን ኢላማ ያደረገ የድሮን ጥቃቶች በአሳሳቢ ሁኔታ እየጨመሩ ይገኛሉ፡፡ የአማራ ማህበር በአሜሪካ ከ22 (ሃያ ሁለት) ያላነሱ የድሮን ጥቃቶች በንጹሃን ላይ መፈጸማቸዉንና በመቶዎች የሚቆጠሩ ንጹሃን ላይ ደግሞ ሞት ማስከተሉን የሚያመለከት ሪፖርት ለመሰብሰብ ችሏል፡፡ የተባበሩት መንግስታት ቢሮ በህዳር ወር በአወጣዉ መግለጫ በአማራ ክልል እየጨመረ የመጣዉ የድሮን ጥቃት እንደሚያሳስባቸዉ የገለጹ ሲሆን14፣ የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ኢታማጆር ሹም የሆኑት ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ በቅርቡ ለመንግስት መገናኛ ብዙሃን በሰጡት ቃለ-መጠየቅ15፣ በንጹሃን ላይ የተፈጸመዉ ግድያ አግባብ ስለመሆኑና የጥቃት ስልቱም በዚሁ አግባብ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልጸዋል፡፡
የሊምኪን የዘር ማጥፋት መከላከል ኢንስቲትዩት መስከረም 12 ቀን 2016 ዓ.ም በአሳተመዉ ጽሁፍ በኢትዮጵያ በአማራ ክልል የዘር ማጥፋት ድርጊቶች በመፈጸም ላይ እንደሆነ አስጠንቅቋል፡፡ ይህ የዘር ማጥፋት ማስጠንቀቂያም በህዳር 30 ቀን 2016 ዓ.ም አድጎና ተሻሽሎ በኢንስቲትዩቱ የቀረበ ሲሆን የኢትዮጵያ መከላከያ ሃይሎች፣ የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት፣ የኦሮሚያ ክልል ልዩ ሃይሎች በተከታታይ የአማራ ብሄር ተወላጆችን መግደላቸዉን፣ የድሮን ጥቃት በንጹሃን ላይ ተጠናክሮ መቀጠሉን፣ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አሁንም በአማራ ክልል ፀንቶ እንደሚገኝ በመጥቀስ አመላክቷል፡፡
ምንም እንኳ የሰብዓዊ ዕርዳታዎች በሃገሪቱ ስራቸዉን እንደገና መጀመራቸዉ ቢገለጽም፣ የሰብዓዊ ድጋፍ ሰጭ ድርጅቶች በአወጡት ሪፖርት መሰረት አሁንም ድረስ በአማራ ክልል ዘልቀዉ መግባት አለማቻላቸዉንና ረሃብ በክልሉ እየተከሰተ እንደሆነ ገልጸዋል፡፡ህዳር 17 ቀን 2016 ዓ.ም የዩኤስ ኤድ ምክትል ረዳት ሃላፊ የሆኑት ቴይለር ቤክልማን ለምክር ቤቱ የዉጭ ጉዳይ በአፍሪካ ንዑስ ኮሚቴ በሰጡት ምስክርነት በአማራ ክልል እየተካሄደ ባለዉ ጦርነት ምክንያት የእርዳታ ሰጭ ድርጅቶች ወደ ክልሉ ዘልቀዉ ለመግባት አለመቻላቸዉን አስረድተዋል፡፡በኢሰመኮ በኩልም በመንገዶች መዘጋት ምክንያት በአማራ ክልል ዉስጥ ለሚገኙ የሃገር ዉስጥ ተፈናቃዮች ሰብዓዊ እርዳታ ለማድረስ አለመቻሉን አሳዉቋል፡፡ ይህ የመንገዶች መዘጋት ድርጊትም ተፈናቃዮች ያለምግብና ዉሃ እንዲቆዩና ለሌሎች የከፋ ችግሮች ተጋላጭ እንዲሆኑ አድርጓቸዋል፡፡ ኢሰመኮ የትኛዉም አይነት ጥቃቶች፣ አለም አቀፍ የሰብዓዊ መብቶች ጥሰቶች፣ ግጭቶች ፣ የዘፈቀደ እስሮች እንዲቆሙ እንዲሁም ኢሰመኮ እና ሌሎች ባለድርሻ አካላት በዘላቂነትና ያለምንም ቅድመ ሁኔታ እስርቤቶችን መጎብኘት እንዲችሉ፣ ያላአግባብ የተያዙና የታሰሩ እንዲለቀቁ፣ የተያዙበት አግባብም ስልጣን ባለዉ ፍ/ቤት እንዲመረመር እንዲደረግ ለመንግስት በሰጠዉ ማሳሰቢያ አሳዉቋል፡፡
በጥቅሉ ከላይ የተዘረዘሩት ማስረጀዎች የሚያሳዩት በአብይ አህመድ መንግስት አሁንም በአለም አቀፍ ደረጃ ጥበቃ የተደረገላቸዉ የሰብዓዊ መብቶች እየተጣሱ መቀጠላቸዉን ነዉ፡፡ በህዳር ወር 2016 ዓ.ም በደቡብ አፍሪካ በነበረዉ አመታዊ ኮንፈረንስ ኢትዮጵያ ወደአጎዋ እንድትመለስ አልተፈቀደላትም፣ እንደ በአፍሪካ የአሜሪካ ንግድ ተጠሪ የሆኑት ኮንስታንስ ሃሚልተን ገለጻም የኢትዮጵያ የአጎዋ አባልነት መታየት የሚቻለዉ ግጭቶችን በሰላማዊ መንገድ መፍታትና የስብዓዊ እርዳታዎች ጉዳት ለደረሰባቸዉ አካባቢዎች መድረስ መቻሉን ስታረጋግጥ ስለመሆኑ አብራርተዋል20፡፡ አሁንም በሃገሪቱ ጦርነቶች እየተካሄዱና መጠነ ሰፊ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች እየተፈጸሙ ባሉበት በዚህ ወቅት ኢትዮጵያን ወደ አጎዋ ተጠቃሚነት መመለስ የተሳሳተ ምልከታ የሚሰጥና በአማራ ብሄር ተወላጆች ላይ እየደረሰ ያለዉን ዘርን መሰረት ያደረገ ጥቃት እንደመደገፍ የሚያስቆጥር ነዉ፡፡
ስለሆነም ከታች ስማቸዉ የተዘረዘሩትን የሲቪል ማህበራት ድርጅቶችን በመወከል፣ የኢትዮጵያ መንግስት በሃገሪቱ እየተካሄደ ያለዉ ጦርነት ባላስቆመበት፣ በአማራ ተወላጆችና ሌሎች ኢትዮጵያዊያን ላይ የሚደርሰዉ ጥቃት በቀጠለበትና ከባድ ወንጀሎችን የፈጸሙ የመንግስት ሃይሎች ተጠያቂ የሚሆኑበት ስርዓት ባልተፈጠረበት ሁኔታ ኢትዮጵያ ወደ አጎዋ አባልነት እንዳትመለስና ታግዳ እንድትቆይ እጠይቀወታለሁ፡፡
የእርሰዎን ለፍትህ፣ ዲሞክራሲና ሰብዓዊ መብቶች ዙሪያ ያልተቋረጠ ጽኑ አቋምም አደንቃለሁ፡፡ የእርሰዎ ይህን ጉዳይ በአንክሮ መመልከት በጦርነት ጥቃት እየደረሰባቸዉና ሰብዓዊ መብታቸዉ እየተገፈፈ ለሚገኙ ኢትዮጵያዉያንም የማይተካ ሚና የሚጫዎት መሆኑን ለመግለጽ እወዳለሁ፡፡
አክባሪዎ
ካሜሮን ዊሂለር
ዳይሬክተር, የመንግስት ግንኙነት
የፋና አባል ድርጅቶች፡-
1. የአማራ ማህበር በአሜሪካ
2. የአሪዞና የአማራ ማህበር
3. የቺካጎ የአማራ ማህበር
4. የአማራ ማህበር በኮሎራዶ
5. የአማራ ባለሙያዎች ህብረት
6. የሎስ አንጀለስ የአማራ ማህበር
7. የአማራ ማህበር በሚቺጋን
8. የአማራ ህዝብ ሲቪክ ድርጅት (ዳላስ፣ ቲኤክስ)
9. የአማራ ማህበር በሲያትል
10. የአማራ ማህበረሰብ Sioux Falls, SD
11. በኦሪገን የአማራ ማህበር
12. የአማራ ማህበር በኔቫዳ
You can find the letter in Amharic here.
Comments